False Guesse Of Woyyaane Caracas

ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀን 2 ሚ. ዩሮ ገቢ ያስገኛል

Posted by Daniel Berhane on Saturday, June 29, 2013 @ 9:57 pm · 2 Comments 

(ናፍቆት ዮሴፍ)

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር ለመቶ አመታት በየቀኑ 2 ሚሊዮን ዩሮ ከኤሌክትሪክ ሽያጭ እንደሚያስገባ ተገለፀ፡፡ ገቢው የኢትዮጵያዊያንን ህይወትና ኢኮኖሚ መልክ ይቀይራልም ተብሏል፡፡

ትላንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ላይ ማንዴላ የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው ሲምፖዚየም ላይ በቀረበው ጥናት፤ ግድቡ በየቀኑ የተጠቀሰውን ያህል ገቢ ከማስገኘቱም በላይ በጎርፍ አደጋ የሚጠቁትን እነ ሱዳንን ከጎርፍ አደጋና ከድርቅ ይታደጋል ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የውሃ ሃብት ኢንስቲትዩት ምሁር ዶ/ር ይልማ ስለሺ፤ “Nile Hydrology and Ethiopian Dams, Great Ethiopian Renaissance Dam – a case study” በሚል ርዕስ ለሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች ባቀረቡት ጥናት፤ የግድቡ መገንባት ከኢትዮጵያ ሌላ ለሱዳንና ለግብፅ እንዲሁም ለአለም ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀው፤ በተለይ ሱዳን ስትቸገር ለኖረችበት የጎርፍ አደጋ ፍቱን መፍትሄ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ የህዳሴው ግድብ ጎርፍንና ፍሰቱን በመቆጣጠር ከአደጋ ከመከላከሉም በላይ 74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ በማጠራቀም፣ ሱዳንና ግብፅ በድርቅ ወራት ሊመጣባቸው ከሚችለው የውሃ ችግር ራሳቸውን ለማዳን ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

ግድቡ ካሉት ጠቀሜታዎች መካከል በየአመቱ በትነት የሚባክነውን ውሃ መቆጠብ አንዱ ሲሆን ድርቅን ለመቋቋም፣ አዲስ የሀይል እድሎችን ለመጠቀም፣ ደለልን ለመቆጣጠርና መሰል ጥቅሞች እንዳሉት ተጠቁሟል፡፡ ግድቡ ከድንጋይ ከሰልና ከነዳጅ የሚለቀቀውን በካይ ጋዝ በመቀነስ የአለምን የሙቀት መጠን (global warming) ለማስተካከል ትልቅ ሚና እንዳለውም ተገልጿል፡፡ በሲምፖዚየሙ ወደ አምስት የሚጠጉ አባይን እና ታላቁን የህዳሴ ግድብ የተመለከቱ ጥናቶች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን አንድ ምሁር ሲምፖዚየሙን አስመልክተው ሲናገሩ፤ “የዛሬው ሲምፖዚየም የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ መንግስታት በቅርበት በመወያየትና ለችግሮቻቸው እልባት በመስጠት ወደፊት የሚራመዱበትን አቅጣጫ ለመወሠን ይረዳቸዋል” ብለዋል፡፡

በሲምፖዚየሙ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩን አቶ አለማየሁ ተገኑን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣አምባሳደሮች፣ባለድርሻ አካላትና የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡ በሲምፖዚየሙ የተሳተፉት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፤ “ጥናቱ ቴክኒካል ቢሆንም ብዙ እንድናውቅ እና አንድ አቋም ስንወስድ በእውቀትና በመረጃ የተደገፈ እንዲሆን ይረዳናል” ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሰላምና የልማት ኢኒስትትዩት ዋና ዳሬክተር አቶ ስብሃት ነጋም፤ ጥናቱ እጅግ አስተማሪ መሆኑን ጠቁመው፤ በአማርኛም ተተርጉሞ ቢሰራጭና ሁሉም ቢያውቀው ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

**********

Source: Addis Admas – June 29, 2013, titled “የህዳሴው ግድብ በቀን 2 ሚ. ዩሮ ገቢ ያስገኛል ተባለ”

Encourage the writer ~

Like this:

Like Loading…
 

Filed under Amharic አማርኛDamEthiopiaGrand Ethiopian Renaissance DamNile Waters

Comments

2 Responses to “ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀን 2 ሚ. ዩሮ ገቢ ያስገኛል”

  1. Bazezew Genanaw says:

    Dear Daniel,
    It is interesting news. I will appreciate if you attach and send me copy of the papers presented.
    If there is similar study on the natural and environmental lifespan of the dam please inform me. As we know, older dams incur higher operational and maintenance costs. Given the nature of our sediment-laden rivers, it is crucial to know more about how the economic lifespan of the dam is assessed.
    Many thanks

     
    0
     
    0

     

     
    Rate This

     

  2. tazabi says:

    There is no doubt one of the many Egyptian billionaires can write a check for that amount of money.


Leave a comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.